Thursday, January 21, 2016

ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን

አፄ ቴዎድሮስን ወልዶ የበላ፤ የአፄ ዮሐንስን
አንገት ያስቆረጠ፤ በእምዬ ምንሊክ ሐውልት ላይ
ቁማር የሚጫወት፤ አባባ ጃንሆይን (ሥዩመ-
እግዚአብሔር) አንግሶ ያዋረደ፤ ቆራጡን መሪ
ጓድ መንግሥቱ ኃይለማሪያምን አንቆራጦ ያባረረ
(በቁሙ አስቀምጦ ቲያትር የሚያሳይ)፤ ታጋይ
መለስ ዜናዊን ያስደነገጠ (አስደንግጦ የገደለ
የሚሉም አሉ)፤እንደሠራ አይገድል!
መሪዎቹን የሚፈራ- መሪዎቹን የሚጠላ
መሪዎቹ የሚፈሩት-መሪዎቹ የማይወዱት ፡፡ (No
love lost between them)
ሠምና ወርቅ የሆነ ሕዝብ ነው፡፡
ይሕ ሕዝብ፡-
ፍቅሩንም ጥላቻውንም በሆዱ የሚፈጅ ምሥጢረ
ሥላሴ የሆነ ሕዝብ ነው፡፡
ይሕ ሕዝብ፡-
አድዋ ላይ ነጭ ተራ ፍጡር መሆኑን ያስመሰከረ፡፡
“ጥቁር ሠው” የሠው ዘር መገኛ ብቻ ሳይሆን
ከሌላው ዕኩል መሆኑን ያረጋገጠ ኩሩ ሕዝብ
ነበር፡፡
ይሕ ሕዝብ፡-
ክፉ ቀንን ያለፈ፤ ከ66 የተረፈ፤ 77 ትንም
97ትንም ያያ… ተአምረኛ ሕዝብ ነው፡፡
ይሕ ሕዝብ፡-
ለኮሪያ የዘመተ፤ ማንዴላን ያሠለጠነ፤ ለአፍሪካ
የነፃነትና የባንዲራ እርሾ ያበደረ… ገራሚ ሕዝብ
ነበር፡፡
ይሕ ሕዝብ፡-
እየሱስ ክርስቶስ ሲጠመቅ ቆሞ የመሠከረ፤
ሞስሊሞች ሲሳደዱ ያስጠጋ፤ በመጽሐፍ ቅዱስ
እስከ ቱንት የተጠቀሰ፤ በቅዱስ ቁራን የተወደሰ፤
በእየሩሳሌም ርስት ያለው፤ለነብዩ መሐመድ አዛን
ያለ፤ የጠገበ መንፈሳዊ ታሪክ ያለው ሕዝብ
ነው፡፡
ይሕ ሕዝብ፡-
የአክሱም ሀውልትን ያቆመ፤ የላሊበላ ውቅር
አብያተ ክርስቲያናትን ያነፀ፤ የጎንደር ቤተ-
መንግሥቶችንና የሐረር ግንቦችን የገነባ አሪፍ
ሕዝብ ነበር፡፡
ይሕ ሕዝብ፡-
ንጉሡ ጥለውት ጠፍተው (ተሰደው) ለራሡ
የጎበዝ አለቃ በመፍጠር ፋሺሽቶችን ተዋግቶ
አገሩን ነፃ ያወጣ፤ መንግሥቱም (ኃይለማሪያም)
ወደ ዚምባቡዬ ሪፈር በተባለ ጊዜ ራሱን በራሱ
ያስተዳደረ ጨዋና ንጉሡ ከሥደት ሲመለሱ
አልጋውን ያስረከበ የዋህ ሕዝብ ነበር
(አይገርምም?)፡፡
ይሕ ሕዝብ፡-
በራሡ ቋንቋ ፍቅሩን አስከመቃብር የጻፈ፤
ሼክስፒርን ፈቶ የመግጠም ፀጋ (ዬ) የተሠጠው
ሕዝብም ነው፡፡
ይሕ ሕዝብ፡-
በቅዱስ ያሬድ በኩል ከሠማየ ሠማያት
የመልአክትን ዝማሬ ሰምቶ ዜማ የሠራ ዜመኛ
ሕዝብ ነው፡፡ (ሞዛርት የለ -ቬቶቨን የት ነበር?
ወፍ የለም)
ይሕ ሕዝብ፡-
ጦርነትን በባዶ እጁ እንዳሸነፈ ሁሉ
ኦሎምፒክንም በባዶ እግሩ ድል ያደረገ ጉደኛ
ሕዝብ ነው፡፡ (ሮም ሁለቴ ጉድ ሆነች እንዳሉት
የአውሮፓ ወሬኞች…)
ይሕ ሕዝብ፡-
የዓባይን ልጅ ውሀ ጠማው ተረቱን እያደሰ
ሱዳንን አልፎ ግብፅን እስከ ሲናይ በርሀ ውሃ
የሚያጠጣ ሳይተርፈው የሚቸር ውሃ የሚያደርግ
ሕዝብ ነው፡፡
ይሕ ሕዝብ፡-
ሌላው የአፍሪካ ሕዝብ የቀኝ ግዛት እባጩ
ንፍፊት ሳይፈነዳለት አብዮት ያፈነዳና እውነተኛው
መንገድ የእኔ ብቻ ነው ብሎ ባላብ አደርና
በወዛደር በእናቸንፋለንና በእናሸንፋለን ጎራ ለይቶ
አንድ ጥይትና ወጣት እስኪቀር ድረስ የሚጫረስ
ግራ የገባው-ግራ -ዘመም ሕዝብ ነበር (ው)፡፡
ይሕ ሕዝብ፡-
ከእናቱ ልጅ ይልቅ በመጽሐፍ ለሚያውቃቸው
አብዮተኞች በማድላት ወንድሙን የሚገድል፤
አገር ለመገንጠልና ለማስገገንጠል እስ-በሱ
የተጫረሰ ጉደኛ ሕዝብ ነው፡፡
የሆነው ሆኖ…
ይሕ ሕዝብ፡-
መሪዎቹን የሚፈራ- መሪዎቹን የሚጠላ
መሪዎቹ የሚፈሩት-መሪዎቹ የማይወዱት ፡፡
ሠምና ወርቅ የሆነ ሕዝብ ነው፡፡
ፍቅሩንም ጥላቻውንም በሆዱ የሚፈጅ ምሥጢረ
ሥላሴ የሆነ ሕዝብ ስለሆነ በቅጡ ግዙት፡፡
ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን

" የትዳር ጓደኛዮን ካሳሁን ግርማሞን የመረጡልኝ እኔ ሳልሆን አለቆቸና የስራ ባልደረቦቼ ነበሩ፡፡" ቴወድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ)

" የትዳር ጓደኛዮን ካሳሁን ግርማሞን የመረጡልኝ እኔ ሳልሆን አለቆቸና የስራ ባልደረቦቼ ነበሩ፡፡" ቴወድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ)

( በይርጉ ፋንታ)
የ16 አመቷ ወጣት ገና ዘላ ሳትጠግብ በሙዚቃ ፍቅር ተለከፈች፡፡ ትምህርቷን ከ4ኛ ክፍል አቋርጣ ፖሊስ ኦርኬስትራን ተቀላቀለች - ጥላየአራጌ፡፡ በወቅቱ በፖሊስ ኦርኬስትራ ውስጥ በውዝዋዜ፣በድምፃዊነት እንዲሁም በተዋናይነት ብታገለግልምይበልጥ ፈርጥ ያደረጋትና ተወዳጅነት ያቀናጃት ውዝዋዜ ነበረ፡፡
ከስራዋ በዘለለ ውሃ የሚደርበው ደም ግባቷ፣ለዛ ያለው ጨዋታዋና ፈገግታዋ በዛው በፖሊስ ኦርኬስትራ ውስጥ ገጣሚና የመድረክ አጋፋሪ (መሪ ) የሆነውን ካሳሁን ግርማሞ በፍቅሯ እንዲወድቅ አደረገው፡፡የኪነት ቡድን ነባር አባል የነበረው ካሳሁን ጥላየን የራስ ሳያደርግ እንቅልፍ ሊይዘው አልቻለም፡፡
ጥላየ ሀምሌ 7/1967 ዓ.ም ፖሊስ ኦርኬስትራን በተቀላቀለች በዚያው አመት በኮሌነል አያሌው አበበ፣ፍሰሀ ሀይሌ (በወቅቱ የአስተዳደር የነበሩ ናቸው) አጋፋሪነት የካሳውን ህልም ዕውን ሆኖ ከጥላዮ ጋር በአንድ ጎጆ መኖር ጀመሩ፡፡
ጥላየ አራጌና ካሳሁን ግርማሞ በተጋቡ በአመታቸው ሀምሌ 7 ቀን 1968 ዓ.ም ወንድ ልጅ ወለዱ፡፡
የልጃቸውን ስም ለማውጣት ብዙ አልተጓዙም፡፡ጥላየ ነፍሰ ጡር ሳለች ደብረ ዘይት አቅንታ ሰዐሊለማ ጉያ የአጴ ቴወድሮስን ስዕል በስጦታ መልክ አበርክቶላትነበር፡፡ለልጇ ስም በምትፈልግበት በዚያን ስዓት ግድግዳ ላይ የሰቀለችውን የአጼቴዎድሮስ ሰዕል ተመለከተች::የአባቱ ስም ካሰሁን ከአጼ ቴወድሮስ ስለተገጣተመላት ቴወድሮስአለችው፡፡
የዛሬውን (ቴዲ አፍሮ) እስከ አምስት አመቱ ልደቱን ከእናቱና ከአባቱ ጋር በመሆን አክብሯል፡፡ ከዚያ ቡኃላበቤተሰቡ መካከል ፍቅር ጠፋ፣ ጭቅጭቅ ነገሰ በመጨረሻም የጥላየ አርጌና የካሳሁን ግርማሞ ትዳር ተበተነ፡፡ ቴዲም ከአባቱ ጋር መኖር ጀመረ፡፡
ጥላየስለትዳሯመበተን ምክንያት ጋዜጠኛ ይጥና ጠይቋት ስትመልስ፡-
" የትዳር ጓደኛዮን ካሳሁን ግርማሞንየመረጡልኝ እኔ ሳልሆን አለቆችና የስራ ባልደረቦቼ ነበሩ፡፡እኔ በዚያ ወቅት የስራ ፍላጎትና የሙያ ፍቅሩ ስለነበረኝ እንዳያባርሩኝ ብዮ እንጂ ስለፍቅርም ሆነ ስለትዳር የማውቀው ነገር አልነበረኝም፡፡"ብላ ነበር፡፡
ወደ አውሮፓ ከሰባት ወንዶች ጋር ትሪኢት ለማቅረብ ተጉዛ ስትመለስ ትምህርቷን 4ኛ ክፍል ላይ ማቆም የትም እንደማያደርሳት ተገነዘበችና ቀን ቀን እየሰራች በማታው ትምህርቷን ቀጠለች፡፡
የጥላየ ትምህርቷን ስታጠናቅቅ የውዝዋዜ ሙያዋን ለቃ የቢሮ ጸሀፊ ስትሆን ካሳሁን የመድረክ መምራት ስራውን ትቶ የፖሊስ ፕሮግራም የሬዲዮ ጋዜጠኛ ሆነ፡፡
ቴዎድሮስ እናቱን በቴሌቨዥን በተመለከተ ቁጥር የአባቱን የወንጀል ታሪከ አተራረክ ስታይል ከአስገምጋሚ ድምጽ ጋር በሬዲዮ በሰማ ቁጥር ወደ ጥበብ እየተሳበ ሄደ - ወደ ሙዚቃ፡፡
በጉርምስና ዕድሜው መግቢያ አካባቢ በግጥም የሞሉ ደብተሮቹን ለእናቱ ሲያሳያት ትናደዳለች፡፡ለአባቱ የሙዚቃ ፍቅሩ ምን ያህል እንደሆነ ሊያስረዳው ይሞክራል፡፡ ካሳሁን በበኩሉ የሙዚቀኛ ሙያ እንደማያዋጣ ሊያስረዳዉ ይሞክራል፡፡
ካሳሁንናጥላየ ልጃቸው ቴዎድሮስ በትምህርቱ በርትቶ ትልቅ ደረጃ እንዲደርስ እንጅ በሙዚቃው እንዲቀጥል አይፈልጉም፡፡ምክንያታቸዉ ደግሞ በመድረክ ላይ ባሳለፋቸው ብዙ አመታት ማትረፍ የቻሉት የአድማጭና ተመልካች አድናቆትና ዝና ብቻ ነዉ፡፡ ልጃቸው እነሱ በከሰሩበት የሂወትመንገድ እንዲከስር አይፈልጉም፡፡ ለልጃቸው የተሻለ ኑሮን ይመኙለታል፡፡
ካሳሁን ግርማሞ ሂወቱ ከማለፉ በፊት አልጋ ላይ ሳለ የቴወድሮስ የሙዚቃ ችሎታ ጓደኝዎቹ ሲያወሩት ኮርቶበት ሂወቱ አልፋለች፡፡ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የዘመኑ የሙዚቃ ንጉስ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም፡፡እናቱ ጥላየ አራጌ ከጥበብ ዉስጥ ወጥታ ወደጥበብ ገብታለች - ቦሌ አካባቢ እቴጌ ጥበብ መደብር ክፍታ እየሰራች ትገኛለች፡፡

New Ethiopian Movie - Yadam Gemena 2015 Full (የአዳም ገመና)

Hareyet ኀረየት - New! Ethiopian Movies 2015 - Full